በተለያዩ የመጽሃፍ ቅዱስ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ጥናት
በየሩብ አመቱ በተወሰነ ርዕስ ላይ የሚደረግ ጥናት
በየቀኑ የሚጠና አጭር ትምህርት
“የዕዝራ ሴሚናሪ ኮርስ ብቻ አልነበረም፣ ጉዞም ነበር። የእዝራ ሴሚናሪ ለእኔ ለውጥ የሚያመጣ ልምድ ሆኖልኛል። ትምህርቶቹ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት እንድመረምር ረድቶኛል። እምነቴ በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፣ እናም ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደምገናኝ እና በህይወቴ ውስጥ ትርጉም እንዳገኝ አስተምሮኛል።”
"ዕዝራ ሴሚናሪ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንዴት የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትና የመለኮትን ፍጹም ፈቃድ ይበልጥ በቃሉ ውስጥ በቀላሉ መረዳት እንደሚቻል መንገድን አሳይቶኛል። ስለዚህ ሴሚናሪ የእግዚአብሔርን ስም እባርካለሁ!!!"
ዕዝራ ሴሚናሪ የእግዚአብሔርን ሕግ ለማጥናትና ለማድረግ፣ ሥርዐቱንና ሕጉን ለማስተማር ራሴን ለመስጠት የረዳኝ ሴሚናሪ ከመሆኑ በተጨማሪ በዚህ ትውልድ መካከል የመንግስቱን መልእክት ለማዳረስ እና ብዙዋች በቃሉ ላይ እንዲመሰረቱ ለማድረግ የሚሰራ ሴሚናሪ በመሆኑ እግዚአብሔርን ስለዚህ አገልግሎት አመሰግነዋለሁ።