Background
About Us
ስለ እኛ

Who We Are


ዕዝራ ሴሚናሪ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት የተመሰረተ ዲጅታል የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ነው። ሴሚናሪ የሚለው ቃል “ሴሚናሪዩም” ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “የችግኝ ማፍያ” ማለት ነው። በእርግጥም ሴሚናሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንደ ዘር የሚዘሩበት፣ ስር ሰደው የሚያድጉበትና የአገልግሎት ፍሬ የሚያፈሩበትንም ልምምድ የሚያገኙበት ነው። የዕዝራ ሴሚናሪ ዲጅታል የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ራዕይና ተልእኮም የዘመኑን የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች በመጠቀም ብዙዎች የዚህ ልምምድ ባለቤት እንዲሆኑ ማገዝ ነው።


Ezra Seminary is a digital Bible school founded on the “Yetnbit Kal Ministries” (Engl. Prophetic Word Ministries). The word 'Seminary' comes from the Latin term 'Seminarium,' which means 'seedbed.' Indeed, the seminary is a place where Bible students are nurtured like seeds, growing deep roots, and bearing fruit through their service. Ezra Seminary's vision and mission are to equip many to become owners of this training by utilizing modern technological tools.

ራዕይ


የዕዝራ ሴሚናሪ ራዕይ የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደ ዕዝራ የእግዚአብሔርን ቃል ለመመርመር፣ በቃሉ ለመኖርና ቃሉን ለመመስከር የቆረጡና የተጉ ሆነው ማየት ነው።

The vision of Ezra Seminary is to see the disciples of Jesus Christ, like Ezra, diligently study, live by, and bear witness to the Word of God, becoming refined and strengthened in their faith.

ተልዕኮ


የዕዝራ ሴሚናር ተልእኮ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ““እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ” (ዮሐ 8፡ 31) ባለው መሰረት በአምላካችን ሕያውና የሕይወት ቃል ለመኖር የሚያስችሉ ትምህርቶችን በድረ ገጽና በስልክ መተግብሪያ ማቅረብ ነው።

The mission of Ezra Seminary is to offer teachings that empower people to live by the living and life-giving Word of God, based on the foundation of Jesus Christ’s words: "If you hold to my teaching, you are really my disciples" (John 8:31). These teachings are made available through both the website and mobile applications, ensuring accessibility for all.

ሦስቱ የሴሚናሪው ዋና ዘርፎች


melak

ዕለታዊ የጥሞና ንባቦች

በየእለቱ ከቅዱስ ቃሉ አጠር ያሉ የጥሞና ንባቦች የሚቀርቡበት፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለሕይወታችን በጸሎት ሆነን ለመስማት የሚያስችለን ነው።

janet

ኮርሶች

በተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርእሶች ጠለቅ ያለ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል ነው።

dawit

ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች

በአንድ መሪ ርእስ ላይ ለሦስት ወራት ጥናት ለማድረግ የሚያስችል፣ እለታዊ ንባብና ሳምንታዊ ትምህርትንም አጣምሮ የያዘ ነው።