Background
በክርስቶስ ማረፍ

በክርስቶስ ማረፍ

3ኛ ሩብ ዓመት 2021

አውሮፕላኑ ከባድ ውሽንፍር አዘል ዐውሎ ነፋስ ማቋረጥ እንዳለበት ካፕቴኑ ከማብረሪያ ክፍላቸው ሆነው እስካስታወቁበት ጊዜ ድረስ በረራው ያን ያህል አስደሳች አልነበረም። “እባክዎ የደኅንነት ቀበቶዎን ያጥብቁ። በፍጥነት ገሥግሰን ማለፍ ይኖርብናል።” የሚል ጠንከር ያለ የማስታወቂያ ድምፅ ከበረራው ክፍል ተሰማ።