የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ሐሳቦች
መስከረም · ጥቅምት · ህዳር · ታህሳስ 2024
በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን በሚገኝ አንድ ሱቅ ውስጥ የፋርስ ምንጣፍ ይታያል። በዚህ ምንጣፍ ላይ ጥንታዊ ደን ተስሏል። ምንጣፉ በስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝን አንድ ትዕይንት በሚያምር ሁኔታ የሚያስቃኝ ነው። ተራሮች፣ ፏፏቴ፣ አረንጓዴና ሰማያዊ ቀለም የሚንጸባረቅበት ሐይቅ፣ በደን የተሸፈኑ ኮረብታዎች፣ እና የደመና ነጠብጣብ የሚታይበት ሰፊው ሰማያዊው ሰማይ ተዘርግቷል። በዚያ ሱቅ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በምንጣፉ ላይ የሚታዩትን ዝርዝር ነገሮች ማለትም፣ በእያንዳንዱ ካሬ ላይ የሚገኙ የክር ቋጠሮዎች ብዛት፣ የምንጣፉን የጨርቅ ዓይነት፣ ጥቅም ላይ የዋሉ ቀለሞችንና ምንጣፉ ላይ ያሉ ሌሎች ደቃቅ ነገሮችን ሁሉ በመመልከት ጊዜውን ማሳለፍ ይችላል። ወይም ሌላው አማራጭ፣ ለምንጣፉ ለየት ያለ ውበት በሰጡት የአሠራር ዘዴዎች እና ጭብጦች፣ ማለትም በሐይቁ ላይ በተንፀባረቀው ሰማይ፣ ተራሮችን በሸፈነው በረዶና የድንጋይ ሽበት በብዛት በሚታይበት አረንጓዴው ደን ላይ አንድ ሰው ትኩረቱን ሊያደርግ ይችላል። የምንጣፉ ዋና ዋና ገጽታዎች እርስ በርሳቸው ውበትን በቅንጅት በሚገለፅ መልኩ፣ በአልፕስ ተራሮች ላይ የሚገኘውን የዚያን ጸጥ ያለ ቦታ ግርማ ያሳያሉ።