Background
ከኢያሱ መጽሐፍ የሚገኙ የእምነት ትምህርቶች

ከኢያሱ መጽሐፍ የሚገኙ የእምነት ትምህርቶች

መስከረም · ጥቅምት · ህዳር · ታህሳስ 2025

መጽሐፈ ኢያሱ ከሙሴ አመራር ወደ ኢያሱ የተሸጋገረበት ጊዜ ላይ ይጀምራል፡፡ የሚጀምረው እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር በመግባታቸው ታሪክ ሲሆን መጨረሻው በዚያች ምድር መስፈራቸው ነው። ኢያሱ በእርግጥም ከባድ የሆነ መንገድን መከተል ነበረበት። ማለትም ሙሴ (ያውም ሙሴካቆመበት መቀጠል ነበር። ያ ግን የትግሉ ጅምር ብቻ ነበር። ኢያሱ ሙሴ ያላደረገውን ማድረግ ነበረበት፡- እግዚአብሔር ከዓመታት በፊት ለአባቶች በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ የተንከራተተውን ሕዝብ ዮርዳኖስን አሻግሮ ወደ ከነዓንም ማስገባት።