ነሃሴ 11
ነሃሴ 17
ቅዳሜ፣
ነሃሴ 11
ዘፀ. 19:1–20:17፣ ራዕይ. 21:3፣ ዘዳ. 5:6–21፣ ያዕቆብ 1:23–25፣ ሮሜ 3:20–24፣ ሮሜ 10:4።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡
“በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል። አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው” ዘፀ. 19:4–6
እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን ከግብጽ ነጻ ካወጣ በኋላ ወዴት መራቸው? ወደ ተስፋይቱ ምድር ወይስ ሌላ ቦታ? በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ መልሱ ምንም ያህል ትክክል ቢሆንም በሥነ መለኮታዊ አመለካከት ስህተት ነው። መልሱን እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ በማለት ይመልሰዋል፡- “ በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል” (ዘፀ. 19:4)። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የስነ-መለኮት መልስ እግዚአብሔር ቅድሚያ የሰጠውና ግቡ ያደረገው ሕዝቡን ወደ ራሱ ማምጣት መሆኑን ይገልጻል።
ሰብአዊ ፍጡራን ከእግዚአብሔር ሲለዩ እርሱ ይፈልጋቸዋል፣ ወደ ራሱም ይጠራቸዋል። ለዚህ መሰረታዊ እውነት ጥሩ ሞዴል የሚሆነው አዳምና ሔዋን ኃጢአት ሰርተውና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ተላልፈው ከእርሱ በተደበቁ ጊዜ በኤደን ገነት የሆነው ነገር ነው። እግዚአብሔር ተነሳሽነቱን በመውሰድ “የት ነህ?” (ዘፍ. 3:9) በማለት ጠራ። እርሱ ሁልጊዜም የመጀመሪያውን እርምጃ ይወስዳል። ኢየሱስ ይህንን ነገር ልብ በሚነካ ሁኔታ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፡- “ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ” (ማቴ. 11:28፣ 29)። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠራናል፤ ዘላለማዊ መዳረሻችን በመልሳችን ላይ ይደገፋል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 17 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ